የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ደብረ መንክራት ቅዱስ አማኑኤል ወሩፋኤል ቤተክርስቲያን የቤተክርስቲያናችን አመሰራረት ፍራንኮንያ መንገድ ላይ በሚገኘው በሄለን ዊልሰን ኮምዩኒቲ አዳራሽ ውስጥ በመሰብሰብ ኪዳን የጀመርነው መስከረም 27 ቀን 2005 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር እንዲሁም ጥቅምት 07 ቀን 2012 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነው። አዳራሹም የተገኘው ያለምንም ክፍያ ለ11 ወራትም ተገልግለንበታል። ቤተክርስቲያናችን በአባታችን በአባ ፍሬሃይማኖት (ቆሞስ) ተቆርቁሮ በዚሁ በፍራንኮንያ መንገድ ላይ በኪዳን ትምህርት ተጀመረ። የቤተክርስቲያኑ ስምም ደብረ መንክራት ቅዱስ አማኑኤል ወሩፋኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተብሎ ተሰይሟል። ከጥቂት ወራትም በኃላ ዲያቆን በመገኘቱ ቅዳሴም እንዲጀመር አስችሎናል። ዲያቆኑም ዲ/ን ካሳሁን ተሰማ ሲባል ከህዳር 23 2005 አ.ም ጀምሮ ለቤተክርስቲያናችን በሊቀ ድቁና እያገለገለ ይገኛል። ከዚያም ከ11 ወራት በኃላ ከጀመርንበት ከፍራንኮንያ መንገድ ቤተክርስቲያናችን አሁንም በድጋሚ በኤድሰል መንገድ በ6200 Indian Run Pkwy ላይ የሚገኝ የሶርያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተገኝቶ በዚያ ቤተክርስቲያን ከጥምቀት 6 ቀን 2013 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጀምሮ በወር 1000 ዶላር እየከፈልን ስንጠቀም ቆይተናል። በ2019 እ.ኤ.አ በ4800 31st Street South Arlington VA ቦታ በእግዚአብሔር ፈቅድ ተገዝቶ በዚህ ስፍራ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል። መልአከ ጽዮን አባ ኃይለጊዮርጊስ – የደብሩ አስተዳዳሪ የቤተ ክርስቲያን አድራሻ - 4800 31st S. Arlington, VA, 22206 ➢ የአሁን ኃላፊ - ቀሲስ ዮሐንስ ኃይሉ ቤተ ክርስቲያን የምትሰጣቸው አገልግሎቶች ዝርዝር ■ Liturgy / ቅዳሴ ወደፊት መረጃ ሲዘጋጅ የሚለቀቅ Read More ■Baptism/ ጥምቀት ወደፊት መረጃ ሲዘጋጅ የሚለቀቅ Read More ■ Wedding /■ ሠርግ ወደፊት መረጃ ሲዘጋጅ የሚለቀቅ Read More ■Weekly Service/ ወደፊት መረጃ ሲዘጋጅ የሚለቀቅ Read More የቅዳሴ መርሃግብር ሁልጊዜ እሁድ 4:00 am-10:00am